Starting Point

Wednesday, 6 March 2013

ከኔ ወዲያ

  ዛሬ ጊዜ መቼም ሳጥን የሚወዱ ዓይነታቸው ብዙ ነው።
አንድ ዓይነት ሁሉንም የሚያደርጋቸው ግን አንድ ጉዳይ አለ።
ሳጥን ውስጥ መቅረት ስለሚፈልጉ፣ ሁሉም ከኔ ወዲያ ባዮች መሆናቸው ነው።
 እስቲ አማርኛችንም ወደ ሳጥን ከመላኩ በፊት፣
የለም እንዳውም እንዳይላክ ስንል
እንናገርበት፥

*

ከኔ ወዲያ  

ነጋ ጠባ እኔ  ማለት

ትልቅ ምንጩ ፍርሃት

 ሆኖ እኮ ነው ብቸኝነት፤

የሚ ኖረው ለጥፋት፣ በጥፋት፤

በድክመት፣ ያለምነት፤


ላይቀር ሞት።

 

ከኔ ወዲያ ማ ይሙት

እየማለ ሲገዘት

 ምኑን አወቆ ስለ መብት፤

ግማሽ ጽዋው የሚሞላው

መች ባወቀው ይኸኛው፣

ለመሆኑ በዛ ማዶው

በ ዚያ ሌላው።

 

መች አርቆ አሰበው፣

ከኔ ባዩ የጎደለው

ግማሽ ጎኑ አምላኩ ነው፤

ባምባው ብቻ የማይገነው፤

 ከኔ ወዲያ የማ ይለው፣

በሁሉም ቤት የሚ ሆነው


 ለ ዝንተ ዓለም የሚዘልቀው።

 

gottlos.pdf Download this file
 

 

 

 

No comments:

Post a Comment