ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ከኃላፊነታቸው ተነሱ
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ለማስተማር ወደ ጀርመን አቀኑ፤
http://www.fetehe.com/themes/bartik/images/186.pdf
***************************እቺ ቺን ሳነባት፥ ጨዋታ አማረኝ፣ ቀልድና ትንሽ ቧልት
እስቲ ልግጠምበት ፥ ቅኔ በበዛበት ባማርኛው ጠላት
ሥልጣን ባልወደደው ጊዜው ባለፈበት። ማነሽ ባለሳምንት፥ የጎደለሽ ትምህርት
ከልጅ አትጫወት ፥ ይወጋሃል ድንገት
አይቀለድ በሳት፥ ያቃጥላል ውበት
ህሊና ካለበት ፥ ካማረው ነፃነት። ለገብሩም አልሆነው ፥ ለሰላም ፈላጊው
ነጋሶም አልበጀው ፥ ሃገር ለመረጠው።
ማን በነገራቸው፥ ዋና ዓይነ ጥላቸው፣
ባንዲራ ሲሰቀል፣ ጨርቅ እያሳየ፣ ጨር ቅ የሚያስጥላቸው፣
ኢትዮጵያን መሆን ነው፥ ኢትዮጵያን መውደድ ነው፣
ዛርና ጋኔሉን የሚያስወጣላቸው፥ የ ሚያ ሳ ብ ዳ ቸ ው።
ዋ ዐ አዐ አ ይ በይ ኢትዮጵያ፥
እእእ እእ ሪ በይ እናቴ
አቤት በይ እትብቴ፣
ኢትዮጵያ ሃገሬ፤
ተስፋሽ ለነገ ነው፣ ባይሆንልሽ ዛሬ።
በቆየውም መተት፣
እስቲ ድገሚበት፣
ላልለ ቀ ቀ ው እብደት
ዛር፣ ጋኔል፣ መዓት ላልወጣለት፣
ፈትለሽ ተዋህደሽ
አሳስረሽ ተብትበሽ
መዓት ልቀቂበት፥ጭንቀት ከራስምታት
ፍርሃት ካዙሪት፥
በእብደት ላይ፤ እብደት ከምሪበት
ክንግዲህ እንደሆ ን አይገዛ አንደበት።
ለባእድ ተገዝቶ፣ ሃገር የሌለው ሰው ባዶ ላደረገሽ
እንኳን እትብትሽን፣ አጽም መቃብርሽን ላስደረመሰልሽ፣
ማረፊያ ማሰቢያ፣ ገዳምሽን ሳይቀር፣ ለሚያሳርስልሽ። እሪ በይ እናቴ
እሪ በይ እትብቴ
ኢትዮጵያ ሃገሬ፤
ተስፋሽ ለነገ ነው፣ ባይሆንልሽ ዛሬ።
/
ታ ድ ያ እ ኮ፣
ቢሆ ንም ፣
ሁሌም !
አይዞኝ ብርሃን ነው፣
እስኪያልፍ ያለፋል ነው፣ሁሉም ሃላፊ ነው፣
በራሱ ሲመጣ፣ ሁሉም ሲደርስበት ዓይኑን ይከፍታል ነው።
No comments:
Post a Comment